በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በቅዳሜና እሁድ ገበያ የ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ፅ/ቤት
no photo

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በቅዳሜና እሁድ ገበያ የእንቁላል ዋጋ በ14 እና 15 ብር በመሸጥ ላይ ሲሆን የሌሎች ምርቶች አቅርቦት በስፋት ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ)

ሀምሌ 2-2017

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በቅዳሜና እሁድ ገበያ መዳረሻዎች የእንቁላል ዋጋ ከ14 እስከ 15 ብር እየተሸጠ ያለ ሲሆን በዶሮ እርባታ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች እና አርሶ አደሮችን በክፍለ ከተማዉ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት እና አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት በማወያየት የመኖ ትስስር እና በክ/ከተማዉ ንግድ ጽ/ቤት በኩል እንዲሁ የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸዉ ጥረት ተደርገበል። በክ/ከተማዉ በ12ቱም ወረዳዎች የእሁድ ገበያ ተግባራዊ በማድረግ ለማህበረሰቡ አማራጭ ገበያን በመፍጠር እየተሰራ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ነዋሪዎች ትኩስ ምርት እንዲያገኙ በማለም አካባቢዉ ከሚገኙ አምራች አርሶ አደሮች፣ የተደራጁ ማህበራት እና ኢንዳስትሪዎችን በማሳተፍ ምርት በቀጥታ ከአምራች ለሸማች እንዲደርስ በክ/ከተማዉ ንግድ ጽ/ቤት በኩል ሰፊ ስራ ተሰርቷል።በተጨማሪም ጠንካራ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።