"አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!"...

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ፅ/ቤት
no photo

"አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!"

ነሃሴ 8-2017

#እንኳን_ደስ_አላችሁ! አቃቂ ዛሬም በድል ደምቃለች! #ለተከታታይ_3አመታት_1ኛ የሆነዉ የክ/ከተማዉ ንግድ ጽ/ቤት እንደ ወትሮዉ ሁሉ ዛሬም 1ኛ ደረጃን በመያዝ አቃቂን የዉጤት ባለቤት አድርጓታል! አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር እለት ከእለት የሚሰሙ የዉጤት ማዕበል እናስተናገደች ሲሆን በዛሬዉ እለት በልዩ ሁኔታ ለተከታታይ 3 አመታት 1ኛ በመዉጣት የክ/ከተማዉ ንግድ ጽ/ቤት ካሉት 11 ክ/ከተሞች መካከል 1ኛ ደረጃን በመያዝ እዉቅና አጊኝቷል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ በላይ ደምሴ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ዉጤት እንዲመጣ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አስተባባሪ ኮሚቴ፣የዘርፉ አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የነጋዴዉ ማህበረሰብ እንዲሁም ነዋሪዎች በተቋሙ ስም አመስግነዋል። ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ) "አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!"