የምርት አቅርቦት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋ......

ዝርዝር ዜና

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ፅ/ቤት
no photo

የምርት አቅርቦት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።

ነሃሴ 8-2017

የምርት አቅርቦት ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ። ነሔሴ 14/2017 ዓ.ም(አቃቂ ቃሊቲ) በአቃቂ ቃሊቲው ክ/ከተማ አስተዳደር የምርት አቅርቦት እና ፍላጎትን ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን እና ሚናቸዉ ወሳኝ መሆኑ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ተዟዙሮ ባደረገው ምልከታ ያነጋገራናቸው ሸማቾች ገልፁ። በአስተዳደሩ በሚገኙ 16 የእሁድ ገበያዎች፤ በአቃቂ የገበያ ማዕከል እንዲሁም በመደበኛ ገበያ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርት አቅርቦትና ፍላጎትና በብዛት፣ በዓይነት፣ በጥራት ከዚህም ባሻገር በተመጣጣኝ ዋጋ ከአምራች በቀጥታ ለሸማቹ ህብረተሰብ ክፍል በመቅረቡ የተረጋጋ የገበያ እንቅስቃሴ መኖሩን ሸማቾች ተናግረዋል። የእሁድ ገበያዎች ለነዋሪዎች በአቅራቢያቸው መኖራቸው አንዱ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩ ባለፈ ትኩስ የአትክልትና ፍራፍሬ፤ የተለያዩ የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶቹ የዋጋ ዝርዝር ወጥቶ መገበያየት መቻሉ ገበያው ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ መሆኑን ጭምር ጠቁመዋል። በእሁድ ገበያ እየቀረቡ የሚገኙ የምርት አቅርቦት የዋጋ ሁኔታ ከመደበኛው ገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር በተመጣጣኝ ዋጋ ግብይት እየፈፀሙ መሆኑን ተናግረዋል። በአጠቃላይ መንግስት ገበያው የተረጋጋ እንቅስቃሴው እንዲኖረው በርካት ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል "አልቆ ለመፈፀም ከህዝብ የተሰጠን አደራ!