የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ስራዎች ዙሪያ የውስጥና የውጪ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ። ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም (አቃቂ ቃሊቲ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ትራንፖርት ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ስራዎች ዙሪያ የውስጥና የውጪ በዛሬው ዕለት የስምምነት ሰነድ የተፈራረመ ሲሆን በሰነዱ ስምምነት የትራንፖርት ቢሮው አቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትግስት እሸቴ፣ የተቋማት ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንፖርት ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትግስት እሸቴ ባለድርሻ አካላትና ተቋማት ለትራንስፖርት ፍሰት መሳለጥ ያላቸው ሚና ጉልህ መሆኑን ገልፀው፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ችግሮችን በመቀነስ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ከብልሹ አሰራር የፀዳ መሆን እንዳለበት፣ ለነጋዴውና ህዝቡ የምሽት ትራንፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ አመላክተዋል፡፡ ስራ አስኪያጇ አክለውም ቅርጫፍ ጽ/ቤቱ በዋናነት የትራንስፖርት አቅርቦት፣ ቁጥጥር እንዲሁም ተርሚናል አገልግሎት በትኩረት እንደሚሰሩ፣ሁሉም ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚገባና ለህዝብ ተጠቃሚነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡